Report
የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባና ዝውውር በአንድ ወጥ፣ ግልጽ፣ ፍትሐዊና ተጠያቂነት ባለው አሠራር እንዲፈጸም አቅጣጫ ሰጠ።
Tikvah EthiopiaFactual
የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባና ዝውውር በአንድ ወጥ፣ ግልጽ፣ ፍትሐዊና ተጠያቂነት ባለው አሠራር እንዲፈጸም አቅጣጫ ሰጥቷል። ዩኒቨርሲቲዎች ከሚኒስቴሩ የምደባ ውጤት ውጭ በራሳቸው ተነሳሽነት ተማሪ መቀበል፣ የተመደበበትን ተቋም መቀየር ወይም ያለአግባብ መመዝገብ እንደሌለባቸው ተገልጿል። የተማሪ ዝውውርም የላኪውና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ የሚፈጸም ሲሆን ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲ ዝውውር አይፈቀድም።